Ethiopia’s first specialized cardiovascular hospital founded by Swedish-trained cardiologist Dr. Fikru Maru
-
Short Code: 9825
-
Emergency Help: 0952343434

እንኳን ደስ አለን… በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው አንጋፋው የልብ ሃኪም ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ለህዳሴው ግድብ ላደረጉት ከፍተኛ አበርክቶ የእውቅና ሰርተፍኬት ተቀበሉ።
ይህን ‘ዳግማዊ ኣድዋ’ የተባለለትን ታላቅ ሃገራዊ ስኬት ለመዘከርና ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች እውቅና ለመስጠት የኢትዮጵያ ኤምባሲ በስዊድን ስቶክሆልም ባዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር ላይ ነው የእውቅናው ስጦታ የተበረከተው። ስጦታውን በዝግጅቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ባለቤታቸው ዶ/ር መሰረት መንግስቱ ተቀብለዋል ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሲመሠረት በወቅቱ በነበሩት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ተመርጠው በተጣለባቸው ሃገራዊ ኃላፊነት መሠረት የግል የጤና ተቋማትን በማስተባበር ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዲሰበሰብ በማድረግ ደማቅ አሻራቸውን ማኖር የቻሉ – ብሄራዊ ኩራትን በፅናት ያረጋገጡ ታላቅ ሰው ናቸው።
“የኢትዮጵያን ልዕልና በከፍታዋ የምናረጋግጥበት ዘመን ኣንዱ ማሳያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነው” በሚል ኣቋማቸው በፅኑ የሚታወቁት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ዛሬ በህይወት ቢለዩንም ጥረታቸው ለስኬት በቅቶ በማየታችን እንኳን ደስ አለን – እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን።
ከአዲስ የልብ ህክምና ማዕከል
