Ethiopia’s first specialized cardiovascular hospital founded by Swedish-trained cardiologist Dr. Fikru Maru
-
Short Code: 9825
-
Emergency Help: 0952343434

አዲስ የልብ ህክምና ሆስፒታል ከጣዝማ የውስጥ ደዌና ቀዶ ጥገና ህክምና ማዕከል ጋር በመተባበር ህዳር 13/2015 ዓ.ም ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ50ሺ ዶላር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስና የ1 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
በድጋፍ መልክ የተበረከተው የህክምና መሳሪያ ለልብ ህክምና እና በተለያዩ አደጋዎች ለሚያጋጥም የአጥንት ስብራት ህክምና አገልግሎት እንደሚውል ድጋፉን በአካል በመገኘት ያስረከቡት የልብ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ገልፀዋል። የተለገሰው አንድ ሚሊየን ገንዘብም የልብ ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ለማሰልጠን የሚውል ነው ብለዋል።
የተደረገውን ድጋፍ አስመልክተው ምስጋና ያቀረቡት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር)፣ በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ የሆስፒታሉን የህክምና አገልግሎት ደረጃ ከፍ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልፀዋል፤ የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ያበረከቱትን አዲስ የልብ ህክምና ሆስፒታል ፣ ጣዝማ የውስጥ ደዌና ቀዶ ጥገና ህክምና ማዕከል እና ዶ/ር ፍቅሩና ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም አብረው ያስተባበሩትን አቶ መላኩ ፈንታን አመስግነዋል።